Result Portal
ሃ ገ ሬ
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
አገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ፣
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።
ሀገሬ ከበዳት
ሀገሬ ከበዳት
የተማሩ ድሆች፤
መሃይም ሀብታሞች፤
ሰካራም ሃያሲ፤
ጉርስ ያጣ ደራሲ፤
ዘራፊ ነጋዴ፤
ሰላም ጠል ወንበዴ፤
ዘረኛ ካደሬዎች፤
ህልም አልባ መሪዎች፤
ሆድ አደር ሰባኪ፤
ዉሸታም አምላኪ፤
ቆብ ቀዳጅ መነኩሴ፤
ተሳዳቢ ቄሴ፤
ትቢተኛ ሼሆች፤
ግር ባይ አማኞች፤
አስመሳይ ተዋናይ፤
የዳኛ ቄል አባይ፤
እኒህ ሁሉ ጉዶች አገር ተሸክማ፤
እንዴት ከፍ ትበል? ከቶ እንዴትስ ትልማ?
የእንግዴ ልጅ
🔍 «የእንግዴ ልጅ» — ለመሆኑ ስሙ ከወዴት መጣ?
ብዙዎቻችን በዕለት ተዕለት ውይይታችን ውስጥ የምንጠቀመው «የእንግዴ ልጅ» የሚለው ስያሜ፣ ለብዙዎች ጥያቄና ውዝግብ ሲፈጥር ይስተዋላል። "ለመሆኑ ከራሷ አካል ለወጣው ልጅ እንዴት ‘እንግዳ’ የሚል ስም ይሰጠዋል?" የሚሉ ጥያቄዎችም ይነሳሉ።
ለመሆኑ የዚህ ስያሜ ምስጢር እና ከጀርባው ያለው አስደናቂ ተፈጥሯዊ እውነት ምንድን ነው? እስቲ አብረን እንመርምረው!
1. «እንግዳ» — ጊዜያዊ ማረፊያ!
በቋንቋችን «እንግዳ» ማለት ወደ አንድ ቤት ለተወሰነ ጊዜ መጥቶ የሚቆይ፣ የቤቱ ዘላቂ አካል ያልሆነ አካል ነው።
- ጊዜያዊ ተልዕኮ፦ የእንግዴ ልጅ (Placenta) በማህፀን ውስጥ የሚፈጠረው ፅንሱ ማደግ ሲጀምር ብቻ ነው። ሕፃኑ በሰላም ተወልዶ ወደዚህ ዓለም ሲቀላቀል፣ የእንግዴ ልጅም ተልዕኮውን ጨርሶ አብሮ ይወጣል። እንደ ማንኛውም የአካላችን ክፍል ሁልጊዜ አብሮን አይኖርም።
- የጊዜያዊ «ድንኳን» ሚና፦ ሕፃኑ በሆድ ውስጥ እያለ የሚመገብበት፣ የሚተነፍስበት እና የሚጠበቅበት ጊዜያዊ ማረፊያ ወይም «የእንግዳ መቆያ» በመሆኑ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።
2. በሕክምናው ዓለም ያለው «እንግዳነቱ»!
ይህ ደግሞ ይበልጥ አስደናቂው ክፍል ነው! በሳይንሱ ዓለም የእንግዴ ልጅ የእናትየዋ ዘላቂ የአካል ክፍል አይደለም።
- የራሱ DNA ያለው አካል፦ የእንግዴ ልጅ የሚፈጠረው ከእናቷ ህዋሳት ሳይሆን፣ ከራሱ ከፅንሱ ህዋሳት ነው። የራሱ የሆነ የጂን (DNA) መዋቅር አለው።
- ስለዚህ በሳይንስም ቢሆን በማህፀን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ተላክኮ የሚቆይ «እንግዳ አካል» እንጂ የእናትየዋ አካል ተደርጎ አይወሰድም።
💡 ባጭሩ ሲጠቃለል…
«የእንግዴ ልጅ» የተባለው ልጅን በማራቁ ወይም በመግፋቱ ምክንያት ሳይሆን፤ ፅንሱ ወደዚህ ዓለም ከመምጣቱ በፊት በማህፀን ውስጥ እንደ «እንግዳ» የሚቆይበት እና ተልዕኮው ሲያበቃ የሚሸኝ ጊዜያዊ የተፈጥሮ ድንቅ ስራ በመሆኑ ነው!
📌 እርሶስ ምን ያስባሉ?
ይህ ስያሜ ተስማሚ ሆኖ አግኝተውታል ወይንስ ሌላ የሚገልጸው አማራጭ ስም ቢኖረው ይመረጣሉ? አስተያየትዎን ከታች ያጋሩን! 👇
(ጽሑፉ ከተመችዎ ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ እውቀቱን ያጋሩ!)
ስልጣንና ጣዕሙ ክፍል ሦስት
የጥርጣሬ ጥላ
የቢሮው ስልክ ተዘጋ። ታምራት ግን አሁንም ስልኩን እንደያዙት በዴንጋጤ እና ግራ በመጋባት
ቆመዋል። ያ ዴምፅ... ያ ዴምፅ ጆሯቸው ውስጥ እያስተጋባ ነው። "ታምሬ" የሚሇውን ቃሌ
የሚጠቀመው አንዴ ሰው ብቻ ነበር። ግን እሱ ከሃያ ዓመት በፊት በነበረው በዚያ አስከፊ ምሽት
መሞቱን በዓይናቸው አይተዋል። ታዱያ ዛሬ ከመቃብር የወጣው ማን ነው?
ረዳታቸው በሩን ከፍቶ ገባ። "ጌታዬ፣ ለምሽቱ ግብዣ የሚለበሰው ልብስ ተዘጋጅቷል። እንዱሁም የክብር
እንግድቹ ዝርዝርም..."
"ውጣ!" ብለው ጮኹ ታምራት። ረዳቱ ደንግጦ ወደኋላ አፈገፈገ። ታምራት አሁን ማንም ሰው
እንዲቀርባቸው አይፈልጉም። በቢሮው ውስጥ ያለት ዘመናዊ ካሜራዎች እንኳ እሳቸውን የሚሰልሉ
መሰላቸው። ያ ቢጫ ፖስታ ውስጥ የነበረው ፎቶ የያዘው ሚስጥር ቀላል አይደለም። በፎቶው ላይ
ካለት አራት ሰዎች መካከሌ ዛሬ በሕይወት ያሉት እሳቸውና ላላኛው ጓደኛቸው አቶ ክፍሌ ብቻ
ናቸው።
ክፍሌን ለማግኘት ወዲያውኑ ስሌካቸውን አነሱና ደወለ። ክፍሌ አሁን የትልቅ ዴርጅት ባለቤት
ቢሆንም፣ በታምራት ስልጣን ጥላ ስር የሚኖር ሰው ነው።
"ክፍሌ፣ ደብዳቤ ደርሶሃል?" አለ ታምራት። ድምፃቸው ይንቀጠቀጣል።
"ምን አይነት ደብዳቤ ታምሬ? ምንም አልደረሰኝም" አላቸው ክፍሌ። "ምነው ደነገጥክ? ዛሬ ምሽት
ታላቁን ድልህን የምታከብርበት ግብዣ አይደለም ወይ?"
"ክፍሌ... ፎቶው ተመልሶ መጥቷል። ያ የጫካው ፎቶ!"
በሌላኛው ወገን ረጅም ዝምታ ሰፈነ። የክፍሌ ትንፋሽ ሲቆራረጥ ይሰማል። "ማን? ማን ነው የላከው?
እሱ... እሱማ ሞቷል አይደል?"
"አላውቅም። ግን ዛሬ ምሽት ግብዣው ላይ እመጣለሁ ብሎኛል። ክፍሌ፣ ይህ ሚስጥር ከወጣ
ሁለታችንም እናልቃለን። ያ ሁለ ህዝብ ፊት የምናሳየው ክብር በአንድ ቀን አመድ ይሆናል" አለ።
ታምራት ስሌኩን ዘግተው ወደ መስኮቱ ተመለሱ። አሁን መስኮቱ ላይ የሚታያቸው ያንቋሸሹትና
የናቁት ህዝብ አይደለም። በየጥላው ስር ሆነው የሚከታተሏቸው ጠላቶች ናቸው። ስልጣን ጣፋጭ
ነበረች፤ አሁን ግን ጣዕሟ ወደ መራራነት እየተቀየረ ነው።
ምሽቱ ደረሰ። የከተማው ባለስልጣናትና ባለሀብቶች በታምራት ግቢ ውስጥ ተሰብስበዋል። ታምራት
በግዳጅ ይመስል እየሳቁ እንግዶችን ይቀበላሉ። ነገር ግን ዓይኖቻቸው የሚፈልጉት አንድን ሰው ነው። በሕዝቡ
መሀል ሆኖ በንቀት የሚመለከታቸውን፣ ያንን የድሮ ሚስጥር የያዘውን ሰው።
በዚህ መሀል አንድ ግዙፍ ሰው ወደ ታምራት ቀረበ። እጁን ለሰላምታ ዘረጋ። ታምራት ሰውየውን
ሲያዩት የያዙት የወይን ብርጭቆ ከእጃቸው አምልጦ መሬት ላይ ተከሰከሰ።
ትናንሽ እርምጃዎች
ትልቅ ተራራን ለመናድ መጀመሪያ ትናንሽ ድንጋዮችን ማንሳት መጀመር ይኖርብሃል። ዛሬ የምታደርጋት አነስተኛ ጥረት፣ የምትማራት አዲስ ክህሎት ወይም የምትጀምራት ትንሽ ስራ ቀላል ልትመስል ትችላለች። ነገር ግን የነገው ትልቅ ስኬትህ መሠረት እሷው ነች። በሂደቱ ላይ እምነት ይኑርህ፤ ዛሬ የምትዘራው ዘር ነገ ማማሩ አይቀሬ ነው!
🌱 በትናንሽ ጅምሮች አትፈር፣ ታገስ፣ በየቀኑ ጥቂት እርምጃ ወደፊት ተራመድ።
ስልጣንና ጣዕሙ ክፍል ሁለት
የማይታየው እጅ
አቶ ታምራት በቢሯቸው መስኮት በኩል የሚያዩትን የከተማዋን ውበት ጥለው ወደ ጠረጴዛቸው
ተመለሱ። በዝግጅት ላይ ያለው የዛሬ ምሽቱ ግብዣ ከፍ ያለ ክብር እንደሚሰጣቸው ያውቃለ። ልክ
ወንበራቸው ሊይ እንዯተቀመጡ ግን ባሌተሇመዯ መሌኩ በቢጫ ፖስታ የታሸገ ዯብዲቤ በጠረጴዛቸው
መሃል ተቀምጦ አዩ።
"ይህንን ማን አምጥቶ እዚህ አስቀመጠው?" ብለው ጮኹ። ረዳታቸው እየተንቀጠቀጠ ገባ። "ጌታዬ...
እኔ አላየሁም፣ ማንም አልገባም" አላቸው።
ታምራት ደብዳቤውን በቁጣ ቀደዱ። ውስጥ ያለው ግን ጽሐፍ ሳይሆን አንዴ የቆየ ፎቶ ነበር።
ፎቶው የዛሬ ሃያ አመት በፊት የተነሳ ነው። ታምራት እና ሶስት ጓደኞቻቸው ምሽግ በሆነ ሰፈር፣
ፊታቸው ላይ ስጋት እየታየ አንድ ትልቅ ቦርሳ ይዘው ይታያለ። በፎቶው ጀርባ ላይ እንዲህ የሚል
ጽሐፍ በደም ቀለም የሚመስል ቀይ ቀለም ተጽፏል፦
"ስሌጣን ላይ ስትወጣ የረገጥከው መሰላል፣ መውረጃህ ሊይ እሾህ ሆኖ ይጠብቅሃል። ያንን ቦርሳና
በውስጡ የነበረውን ሚስጥር ረሳኸው ታምሬ?"
ታምራት ትንፋሻቸው ተቆረጠ። "ታምሬ" ብሎ የሚጠራቸው ያ የዴሮ ጓደኛቸው መሞቱን እርግጠኛ
ነበሩ። እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ስልኩን አነሱ። የደህንነት ክፍሉን በመጥራት አስበው ግን ተዉት። ይህ
ሚስጥር ከወጣ ስልጣናቸው ብቻ ሳይሆን ህይወታቸውም እንደሚያከትም ያውቃሉ።
በዚህ መሃል የቢሮው ስሌክ አቃጨለ። "ሄሎ" አሉ።
ዴምፁ ቀዝቃዛ ነው... "ጣዕሙ እንዴት ነው ታምራት? ገና መራራው ክፍሌ አልደረሰም። ዛሬ ምሽት
ግብዣህ ላይ እገኝ ይሆናል" ብሎ ተዘጋ።
ታምራት ቢሯቸው ውስጥ ብቻቸውን ሆነው ላባቸው ይፈስ ጀመር። ያንቋሸሹት ህዝብ ሳይሆን፣
የቀበሩት ታሪክ አፋቸውን ከፍቶ ሊውጣቸው እንደመጣ ተገነዘቡ......
ይቀጥላል.......
ታማኛለች ቀርፋፋ ነው እያለች ፤ አላወቀችም ከብዙ ቀን ጥርቅም በኋላ መራመድ እንደሆነልኝ ፤ ተዓምር ሆኖ ባርቆብኝ ፣ ደክሞኝ እየተራመድኩ እንደሆነ ብታውቅ መንቀራፈፌ ሳይሆን መራመዴ ትንግርት ይሆንባት ነበር!
ደግሞ አሮጌ ጨርቅ ማጥለቄ ደህይቼ መስሏታል ፤ ከጎዳና ላይ ተነስቼ ከብጭቅጫቂ ጨርቅ ወደ አሮጌ ጨርቅ ማደጌን ብታውቅ ደህይቼ ሳይሆን እያለፈለኝ መሆኔን ትገነዘብ ነበር።
ትክ ብዬ ማየቴ ድፍረት ነው የመሰላት ፤ አንገቴን ደፍቼ መኖሬን ብታውቅ ቀና ከማለት አድጌ በልበ-ሙሉነት ማየቴ ድፍረት ሳይሆን ልበ-ሙሉነቴ አድጎ እንደሆነ ትመሰክርልኝ ነበር ።
እግረመንገዱን የመጣ መዛኝ እየመዘነ ነው የሚያስቀን !
ችላ ስትለኝ ችላ ማለቷን ከቁብ ያለመቁጠር ንቀት ነው የመሰላት ግን አይደለም ፤
የስህተታችን ጅማሬ በሁሉም ሰው ተቀባይነት ለማግኘት መዳከር ነው የሚለው ጥበብ ገብቶኝ እንጂ ።
እኔ ግን ትግሌ ከራሴ ትናንት ጋ ነው!!!
@keye_ber
ስልጣንና ጣዕሙ
ስልጣንና ጣዕሙ ክፍል አንድ
አቶ ታምራት ጥቁር መስታወት ባለው ዘመናዊ መኪናቸው ውስጥ ሆነው በመስኮት ወደ ውጭ
ይመለከታለ። መንገደ በሰዎች ብዛት ተጨናንቋል። ፀሃዩ የበረታበትና ላባቸውን በክንዳቸው የሚጠረጉ
ሰራተኞች፣ ቅርጫት የተሸከሙ እናቶች፣ እና አቧራ የለበሱ ህፃናት በመንገደ ግራና ቀኝ
ይተማመታሉ።
ታምራት ፊታቸውን አኮሳተሩ። "ይህ ሁለ ህዝብ የት ነው የሚሄደው? መንገደን እንዱህ
የሚያጨናንቁት ስራ ስለሌላቸው ነው" አለ። አብሯቸው የነበረው የግሌ ረዲታቸው። ዴምፃቸው ውስጥ
ከፍተኛ ንቀት ይንጸባረቃል። ከጥቂት አመታት በፊት ምርጫ ሲቃረብ፣ በእነዚሁ ሰዎች ሰፈር እየተገኙ
"እኔ የእናንተ ሌጅ ነኝ፣ ለውጥ አመጣለሁ" እያለ ጎንበስ ብልው ሲማጸኑ የነበሩት ታምራት፣ ዛሬ
በህዝቡ መሀል ማለፍ እንደ መርገም ቆጥረውታል።
ለእሳቸው ህዝብ ማለት ስልጣን ሊይ እስኪወጡ የሚጠቀሙበት "ቁጥር" ብቻ ነው። አንዴ ወንበሩ ላይ
ከተሰየሙ በኋሊ ግን ህዝቡ ለታምራት የሚታያቸው እንደ አሊስፈሊጊ ጩኸት እና እንደ አቧራ ነው።
ቢሯቸው ደረሱ። ቢሮው ውስጥ ያለው ቅንጦት ከውጭ ካለው ድህነት ጋር ሰማይና ምድር ነው። አቶ
ታምራት ወንበራቸው ሊይ ዘና ብለው ተቀመጡ። ስልጣን ጣፋጭ ናት፤ ግን ይህቺን ጣዕም ለማቆየት
ህዝብን ማንቋሸሽ፣ ተቃዋሚን ማሳደድ እና የመንግስትን ሀብት እንደ ግል ንብረት መጠቀም ግዴታ
እንደሆነ ያምናሉ።
ዛሬ ጠዋት አንድ አስቸኳይ ትእዛዝ አስተላለፉ። "ከቢሮዬ ፊት ለፊት ያሉትን ትናንሽ ሱቆች በሙሉ
አንሱ፤ አካባቢውን ያቆሽሹታሉ" አሉ። እነዚያ ሱቆች በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን
እንደሚያስተዳድሩ ግዴ አልሰጣቸውም። ለእሳቸው ውበትና ስልጣን እንጂ፣ የሰው ልጅ ህይወት
ትርጉም የለውም።
ታምራት ስልኩን አነሱና ወደ ቤታቸው ደወሉ "ዛሬ ማታ ትልቅ ግብዣ አለኝ፣ ከውጭ የመጣ ውድ
ወይን ተዘጋጅቷል?" ብለው ጠየቁ። በችጋርና ረሃብ የተጠበሰው፣ትናትና ከኑሮ ውድነት እንዱሁም
በግፍ ከመገደል እና ሃገር ጥል ከመሰደድ ይታደጉናሌ ብለው የመረጡት ህዝብ ግን ለዳቦ በሚሰለፍበት
ሰዓት፣ታምራት በስልጣን ጣዕም ሰክረዋል። ነገር ግን ይህ ጣፋጭ ስልጣን መራራ ውጤት ይዞ
እንደሚመጣ ገና አላወቁም ነበር፡፡
ይቀጥላል.......
ስልጣንና ጣዕሙ ክፍል አንድ
ሳያቋርጡ_ጥረት_ማድረግ (ወጥነት) (consistency
በተራራው ጫፍ ላይ የመውጣት ዓላማ ኖሮህ ከተራራው ስር ተቀምጠህ ሽቅብ ወደላይ ስታየው መውጣት ፈፅሞ የሚቻል ላይመስልህ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከተቀመጥክበት ተነስተህ የመጀመሪያውን እርምጃ ስታደርግ ከተቀመጥክበት አንድ እርምጃ እየራቅክ ወደ ተራራው ጫፍ አንድ እርምጃ እየቀረብክ ነው ማለት ነው፡፡
እርምጃህን ሳታቋርጥ ሽቅብ መጓዝህን ብትቀጥል ከብዙ እርምጃዎች በኋላ ራስህን በተራራው ጫፍ ላይ ልታገኝ ትችላለህ፡፡ እንደት ባለ ሁኔታ ይኼንን አስፈሪ ተራራ እንደወጣህ ከተራራው ጫፍ ላይ ሆነህ ትገረማለህ፡፡
ዛሬ የ2018 ዓ.ም ሐምሌ 3 ነው፡፡ ዓመቱ እያለቀ ነው። በዚህ ዓመት አሳካዋለው ብለህ ያቀድከውን ዕቅድ ገምግመህ ለቀጣዩ የዓመት ዕቅድህን አንድ ብለህ ማቀድ እና መዘጋጀት ትችላለህ፡፡ በዚህ ውሳኔህ ከፀናህና ሳታቋርጥ "consistently" ዕቅድህን መተግበር ከቻልክ የዓመቱን ዕቅድህን ከማሳካት ወደ ኋላ አትመለስም፡፡
የዛሬው ጥረትህ ብቻዋን ከምንም የማትቆጠር ትንሽዬ ተግባር ሆና ልታገኛት ትችላለህ፡፡ ነገር ግን የየቀኑ ትንንሽ ተግባራት ድምር ውጤት ትልቅ ተግባር ይሆናል። ስለዚህ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ለማሳካት ስላሰብከው ትልቅ ውጤት ማሰብህን ለጊዜው አቁመህ የዛሬ ተግባርህን ለራስህ #ታማኝ ሆነህ መተግበር ጀምር፡፡
ቀስ በቀስ ወደ ስኬትህ እየቀረብክ አሁን ካለህበት እየራቅክ እንደሚትሄድ አውቀህ ዛሬውኑ ጀምር፣ ነገም ቀጥልበት፣ ከነገ ወዲያም አታቋርጥ፡፡ ከሳምንት ወደ ሳምንት፣ ከወር ወደ ወር ሳታቋርጥ ጥረት በማድረግ ከተነሳህበት መነሻ እየራቅክ ወደ መዳረሻህ እየቀረብክ መምጣትህ የማይቀር ነው፡፡
እግዚአብሔር በነገር ሁሉ መከናወንን ይስጠን!
ስልጣንና ጣዕሙ
"ስልጣንና ጣዕሙ" የሰው ልጅ በስልጣን ጥም፣ በክህደትና በእውነት መካከሌ የሚያደርገውን ውስብስብ
ትግል የሚዲስስ ታሪክ ነው። ታሪኩ የሚጀምረው ከከፍታ ማማ ላይ ሆኖ ዓለምን በሚገዛው አቶ
ታምራት ቢሆንም፣ በውስጡ ግን ለሃያ ዓመታት ተቀብሮ የቆየ የጨለማ ምስጢር ይዟል።
በዚህ መጽሏፍ ውስጥ፣ ስልጣን እንደ ማር የጣፈጠቻቸው ባለስልጣናት በክህደት የገነቡት ህንፃ
በእውነት ማዕበል ሲናድ እንመለከታለን። ያለፈ ታሪክ ምንም ያህል ቢቀበር፣ ትክክለኛ ሰዓቱን ጠብቆ
ዳግም መውጣቱ የማይቀር መሆኑን ታሪኩ በዝርዝር ያሳያል። "ቀይ ብዕር" የተባለው ምስጢራዊ ገፀ-
ባህሪ ደግሞ፣ የፍትህ መዛግብት በዝምታ ቢፃፉም መጨረሻቸው ግን ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን
የሚያሳይ የጽናት ተምሳሌት ነው።
የጽሐፉ መልዕክት፡
የሥነ-ምግባር ትምህርት መስጠት
የፍትህና የእውነትን ዋጋ ማጉላት
የሰው ልጅን ውስጣዊ ማንነት መመርመር
አንባቢን ማዝናናትና ማሳተፍ
ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አስራ አራት
ጠቃሚ የህይወት ምክር እና አባባሎች
👉 ሰዎች የሰጡህን ዘውድ ሳይሆን ጭንቅላትህን በአግባቡ ተጠቀም።
👉 ክብርና ብር ለሚገባው እንጂ ለሚፈልግ ሁሉ አይሰጥም።
👉 ያስታወሱህ ስለቀረህ ሳይሆን ያንተን ቦታ ሚሽፍን ስላጡ ነው።
👉 አመስጋኝ ላልሆነ ሰው ማር ብትሰጠው አንተን ሳይሆን ማሩን የሰራችውን ንብ ያደንቃል።
👉 ምናለ የነገሮችን መጨረሻ ሳንጀምር ብናውቅ።
ሥራ እንደ ሕይወት ፍልስፍና
እያንዳንዱ የምንሠራው ሥራ ከዕለት ጉርስ ማግኛነት ባለፈ የውስጣችንን ማንነት፣ ትዕግሥት እና የጥበብ ጥማት የምናሳይበት ትልቅ መድረክ ነው ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ሥራ ማለት እንዲሁ ዝም ብሎ የሚከናወን ሜካኒካዊ ተግባር ሳይሆን፣ ከአእምሮ ፍልስፍና ተነሥቶ በእጆች የሚቀረጽ ሕያው ጥበብ ነው።
በተለይ በእንጨት ሥራና በዕደ-ጥበብ (Art & Crafts) ዓለም ውስጥ ስንቀሳቀስ ሥራን ከሕይወት ፍልስፍና ጋር የማገናኝባቸው ሦስት ዋና መርሆዎች አሉኝ፦
1. ትዕግሥት እና ጥንቃቄ (Patience & Precision)
አንድን ሸካራ እንጨት አልምዶ፣ መልክ አስይዞና ጥራት ባለው መልኩ አውጥቶ ለዓይን የሚማርክ የብርሃንና የውበት መገለጫ ማድረግ የሚቻለው በትዕግሥት ብቻ ነው። ሕይወትም ልክ እንደዚሁ ናት፤ ጥሬ ዕቃዋን በትዕግሥትና በጥንቃቄ ካልቀረጽነው የምንፈልገውን ውብ ውጤት አናገኝበትም።
2. የፈጠራ ነጻነት (Creative Freedom)
ጥበብ ካለፈው ልምድ እየተነሣች አዲስ ዕይታን የምትፈጥር ነፍስ ናት። በምሠራቸው የእጅ ሥራዎች ሁሉ ውስጥ "የፊኒሽንንግ ሥራዎችንና የእንጨት ሥራዎችን" አንዳንዴ ደግሞ "የቀይብዕር ዲያሪ" በተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያ ጥልቅ የጥበብ እና የእውቀት ማረፊያ ሐሳብ ለማንጸባረቅ እጥራለሁ። እያንዳንዱ የተጠናቀቀ ሥራ የራሱ የሆነ ታሪክና ፍልስፍና እንዲኖረው ማድረግ የዘወትር ፍላጎቴ ነው።
3. ታማኝነትና ጥራት (Integrity & Excellence)
የእጅ ጥበብ ሥራ ትልቁ መለኪያው ከውስጥ የሚመነጭ ታማኝነት ነው። ሰው ቢያየውም ባያየውም፣ ከውስጥ የሚደረገው ጥንቃቄና ለሥራው የሚሰጠው ክብር የውጤቱን ጥራት ይወስነዋል። የምንሠራው ሥራ የእኛ መስታወት ነው።
ይህ "ሥራና ፍልስፍና" የተሰኘው ክፍል፣ በሥራዎቻችን ውስጥ የምናሳየውን ጥረት፣ የምንቀስመውን እውቀት እና የሕይወትን ጉዞ የምንመረምርበት የጋራ መወያያ መድረካችን ይሆናል።
የእናንተስ የሥራ ፍልስፍና ምንድን ነው? በዕለት ተዕለት ሥራችሁ ላይ ትልቁ መመሪያችሁ ምንድን ነው? አሳቡን በኮሜንት አጋሩኝ!
የንስር ሕይወት ትምህርት
ይህን ያውቁ ኖሯል? ከሁሉም ወፎች መካከል ንስርን ለመረበሽ የሚደፍር ቁራ ብቻ ነው። ንስር ይኼን ስታይ 👉 ጥበብ ትጠቀማለች። ቁራውን ተመልሳ ለማጥቃት በፍፁም አትጨነቅም፤ ይልቁንም ስለ ራሷ ጥንካሬ እና ስኬት ጥልቅ እውነት ታሳየናለች።
ቁራ ያለ አንዳች ሃፍረት በንስር ጀርባ ላይ አርፋ ሰላም ትነሳታለች፣ የንስርን ላባ ትነጫለች፣ ትረብሻለች፣ ታናድዳታለች፣ ሳታቋርጥ እረፍት ትነሳታለች።
ነገር ግን ንስር ጉልበቷን በቁራ ንዝነዛ አታባክንም። አላስፈላጊ ትግል አታደርግም። የበቀል እርምጃም አትወስድም። ነገር ግን ንስር አንድ ውሳኔ ትወስናለች፤ ሙሉ ኃይሏን ተጠቅማ ወደ ላይ ወደ ከፍታ ትወጣለች።
ከፍታ ብቻ ነው ከቁራ ጋር የገጠማትን ችግር የሚፈታው። ንስር ወደ ላይ ከፍ እያለች በሄደች ቁጥር ቁራ አየር እያጠራት፣ መተንፈስ እያቃታት፣ መድከም ትጀምራለች። በመጨረሻም ንስሯን ትታ ለመውደቅ ትገደዳለች። እውነተኛ ድል የሚገኘው ከፍ ብሎ በመነሳት ውስጥ እንጂ ከሚነዘንዙህ ጋር ግብግብ በመፍጠር አይደለም፤ ለአሉባልተኞች መልስ በመስጠትም አይደለም። ስላንተ ስያወሩ ውለው ቢያድሩ እንኳን እንዳላየህ፣ እንዳልሰማህ ሆነህ ዝም በላቸው። ንስሯ ተዋግታ አላሸነፈችም። በቀላሉ ከፍ በማለቷ ብቻ ቁራ ራሱን ሊያጠፋ ችሏል።
ይህንን እወቅ፦ ሌሎች ይናቁህ፣ ይናገሩ፣ ይውቀሱህ፣ ይተቹህ፣ ይሳለቁ። አንተ ግን እነሱን ለመገዳደር ስባል ጊዜ አታባክን፤ የፈለጉትን ያድርጉ። ይልቁን ለማደግ ፣ ለመራመድ ፣ አዲስ ከፍታ ላይ ለመድረስ ተንቀሳቀስ።
ምክንያቱም እውነታው እዚህ ጋር ነው፡- ሰዎች አንተ የደረስክበት ከፍታ ላይ መድረስ አቅቷቸው ይተዉሃል። ምንም ሳይሆን ከፍታህ ብቻ ጩኸታቸውን ጸጥ ያደርጋል። ወደ ታች ለመነታረክ ዝቅ አትበል፤ ወደ ላይ ማደግህን ቀጥል!
አሥሩ (10) የውጤታማ መሪዎች ባህሪያት
#የመሪነት_ደረጃዎን_ከፍ_ማድረግ_ይፈልጋሉ?
ሰዎችን ለማነሳሳትና በመሪነት ስኬትን ለማምጣት የሚረዱ አስር የውጤታማ መሪዎች ባህሪያትን ቀጥለን እንመልከት🚀
1. 👉#የጠራ_እይታ (Clear vision)
መሪ ተከታዮችን ወዴት እየመራ እንደሆነ የጠራ ዓላማና ግልፅ ራዕይ ከሌለው እየመራ ሳይሆን እያደናገረ ነው ልንል እንችላለን። መሪ ስለተሰጠው ኃላፊነትና ስለሚመራው ተቋም ግልፅ ርዕይ ያለው ሊሆን ይገባል። ይኼ ካልሆነ በተቋሙ ውስጥ ቀደም ሲል የነበረውን አሰራርና ተቋማዊ ባህል (status quo) ከማስቀጠል ውጪ ልዩነት የሚፈጥር አዲስ ነገር ይዞ መምጣት አይችልም።
2. 👉#ውጤታማ_ተግባቦት (Effective communication)
መሪ የሚያስበውን ሀሳብ ግልፅና አሻሚ ባልሆነ መንገድ ማስረዳትና ማሳመን የሚችል፣ ለተግባቦት ጠንቅ የሆኑ አሉታዊ ሀሳቦችንና ቃላትን የማይጠቀም፣ ለስራ የሚያነሳሳና የሚያበረታታ፣ ገንቢ ግብረ መልስ የሚሰጥ፣ ጥሩ አድማጭና ውጤታማ የተግባቦት ክህሎት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡
3. 👉#ለዓላማ_ያለው_ታማኝነት (Integrity)
መሪ ከግል ፍላጎቱ ይልቅ የጋራ ዓላማን በማስቀደም ለሚመራቸው ሁሉ ጥሩ ምሳሌ መሆን መቻል አለበት፡፡ መሪው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳ እየመራ ያለ ቢሆን ሐቀኝነቱንና መልካም ምግባሩን መጣል የለበትም፡፡ ምክንያቱም ታማኝነት (integrity) ሲጎድል መሪነት ማብቅያው ይሆናልና፡፡
4. 👉#ሌሎችን_ማብቃት (Empowering others)
በሌሎች ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም እንዲያወጡና እንዲጠቀሙ ማስቻል የመሪነት ተፅዕኖ መፍጠሪያ ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ መሪዎች ተከታዮቻቸው የሚማሩበት፣ የሚያድጉበትና መሪነትን የሚለማመዱበት ምቹ ከባቢ (environment) በመፍጠር እውነተኛ ለውጥና እድገት እንዲመጣ ማድረግ አለበት፡፡
5. 👉#ውሳኔ_ሰጪነት (Decision making)
ሁኔታዎች በቅጽበት በሚለዋወጡበት፣ አጠራጣሪ ነገሮች በሞሉበት ዓለም ላይ ሳያወላውሉ ውሳኔ እየሰጡ መምራት የመሪውን ተፅዕኖ የመፍጠር ደረጃን ከፍ ያደርጋል፡፡ ውሳኔ የመስጠት እርምጃ በተሳታፊዎች ብቃት፣ በመረጃና በጊዜ ላይ ጥገኛ በመሆኑ ተገቢውን መረጃ በማጣራት አሳታፊና ወቅቱን የጠበቀ ውሳኔ መስጠት መቻል ከመሪዎች የሚጠበቅ ነው፡፡
6. 👉#ስሜትን_መገንዘብ (Emotional awareness)
መሪ ከሌሎች አብሮ ሰራተኞች አንዱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመሆኑም የሌሎችን ህመም አይቶ ባላየ የሚያልፍ ሳይሆን ለሌላው ደህንነት የሚያስብ፣ የሚሰማቸውን ስሜት እንዲያንፀባርቁ እድል የሚሰጥ፣ በሀዘንም ሆነ በደስታ ከተከታዮች ጎን የሚቆም፣ ስሜታቸውን የሚረዳ ሊሆን ይገባል፡፡
7. 👉#ኃላፊነት_መውሰድ (Taking responsibility)
እውነተኛ መሪዎች ለግል ስህተታቸውም ሆነ ለቡድኑ ውድቀት ኃላፊነት የሚወስዱ እንጂ የሚሸሹ አይደለም፡፡ ግልፅ የሆኑ የአፈጻጸም ግቦችን (performance expectations) በማስቀመጥ ሰዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ያበረታታቸዋል፡፡ ተከታታይ መሻሻልና የአፈፃፀም ብልጫ እንዲኖር በተጠያቂነት መንፈስ ይንቀሳቀሳል፡፡ ኃላፊነትን የሚወስድ መሪ ስኬት ሲኖር "የእኔ" ስህተት ሲኖር "የእነሱ" የሚል አይደለም።
8. 👉#ለውጥን_መላመድ (Adapting to change)
በዓለም ላይ የማይቀር ብቸኛ ቋሚ ነገር ለውጥ ነው፡፡ ለለውጥ ያልተዘጋጀ መሪ ከጊዜው ጋር አብሮ መጓዝ አይችልም፡፡ ሁኔታዎች ሲቀየሩ ከሁኔታዎች ጋር አብሮ የሚሄዱ ስልቶችን መንደፍ፣ ፈተናዎችንና ውድቀቶችን እንደ መማሪያ እድሎች የሚወስድ መሪ ውጤታማ ሆኖ የሚቀጥል ነው፡፡
9. 👉#የቡድን_መንፈስ_መገንባት (Building team spirit)
የተባበረና የተነቃቃ ቡድን መገንባት ያልቻለ መሪ ወደፊት ለመጓዝ እግሩ ይያዛል፡፡ መሪ የቡድኑን የጋራ ማንነት፣ ጓዳዊነትን በማጠናከር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ የሆነ ቡድን መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡ ትልቅም ሆነ ትንሽ የተገኙ ድሎችን በጋራ የማክበርና የመመሰጋገን ባህልን ማጠናከር መሪው የቡድን መንፈስን ለመፍጠር ያግዛል፡፡
10. 👉#ግጭቶችን_መፍታት (Conflict resolution)
ውጤታማ መሪዎች ግጭቶችን የሚያስወግዱ ሳይሆን ውጤታማ በሆነ መንገድ የቡድኑን አንድነት ሳይረብሽ እንዲፈታ መንገድ የሚቀይሱ ናቸው፡፡ የችግሮችን ምልክቶች ለማጥፋት ብቻ ሳይሆን ዋናውን መንስኤ የሚፈታ ዘላቂ መብትሔ በማፈላለግ ላይ ያተኩራሉ፡፡
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ አስር ባህሪያትን የራሱ ያደረገ መሪ በመሪነት ደረጃው ከፍ ያለ ተፅዕኖ የማያሳድርበትና ለውጥ የማያመጣበት ምክንያት አይኖርም፡፡ የእርስዎን አመራር ሂደት በደንብ ይፈትሹና ለማስተካከል ይሞክሩ፡፡
popular post
-
👉 ሰዎች የሰጡህን ዘውድ ሳይሆን ጭንቅላትህን በአግባቡ ተጠቀም። 👉 ክብርና ብር ለሚገባው እንጂ ለሚፈልግ ሁሉ አይሰጥም። 👉 ያስታወሱህ ስለቀረህ ሳይሆን ያንተን ቦታ ሚሽፍን ስላጡ ነው። 👉 አመስጋኝ ላልሆነ ሰው ...
-
የንስር ሕይወት ትምህርት ይህን ያውቁ ኖሯል? ከሁሉም ወፎች መካከል ንስርን ለመረበሽ የሚደፍር ቁራ ብቻ ነው። ንስር ይኼን ስታይ 👉 ጥበብ ትጠቀማለች። ቁራውን ተመልሳ ለማጥቃት በፍ...
-
እያንዳንዱ የምንሠራው ሥራ ከዕለት ጉርስ ማግኛነት ባለፈ የውስጣችንን ማንነት፣ ትዕግሥት እና የጥበብ ጥማት የምናሳይበት ትልቅ መድረክ ነው ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ሥራ ማለት እንዲሁ ዝም ብሎ የሚከናወን ሜካኒካዊ ተግባር ...
-
የጥርጣሬ ጥላ የቢሮው ስልክ ተዘጋ። ታምራት ግን አሁንም ስልኩን እንደያዙት በዴንጋጤ እና ግራ በመጋባት ቆመዋል። ያ ዴምፅ... ያ ዴምፅ ጆሯቸው ውስ...
-
#የመሪነት_ደረጃዎን_ከፍ_ማድረግ_ይፈልጋሉ? ሰዎችን ለማነሳሳትና በመሪነት ስኬትን ለማምጣት የሚረዱ አስር የውጤታማ መሪዎች ባህሪያትን ቀጥለን እንመልከት🚀 1. 👉#የጠራ_እይታ (Clear vision) መሪ ተከታዮች...









