የንስር ሕይወት ትምህርት

ይህን ያውቁ ኖሯል?  ከሁሉም ወፎች መካከል ንስርን ለመረበሽ የሚደፍር ቁራ ብቻ ነው። ንስር ይኼን ስታይ 👉 ጥበብ ትጠቀማለች። ቁራውን ተመልሳ ለማጥቃት በፍፁም አትጨነቅም፤ ይልቁንም ስለ ራሷ ጥንካሬ እና ስኬት ጥልቅ እውነት ታሳየናለች።


ቁራ ያለ አንዳች ሃፍረት በንስር ጀርባ ላይ አርፋ ሰላም ትነሳታለች፣ የንስርን ላባ ትነጫለች፣ ትረብሻለች፣ ታናድዳታለች፣ ሳታቋርጥ እረፍት ትነሳታለች። 

ነገር ግን ንስር ጉልበቷን በቁራ ንዝነዛ አታባክንም። አላስፈላጊ ትግል አታደርግም። የበቀል እርምጃም አትወስድም።  ነገር ግን ንስር አንድ ውሳኔ ትወስናለች፤ ሙሉ ኃይሏን ተጠቅማ ወደ ላይ ወደ ከፍታ ትወጣለች።


ከፍታ ብቻ ነው ከቁራ ጋር የገጠማትን ችግር የሚፈታው። ንስር ወደ ላይ ከፍ እያለች በሄደች ቁጥር ቁራ አየር እያጠራት፣ መተንፈስ እያቃታት፣ መድከም ትጀምራለች። በመጨረሻም ንስሯን ትታ ለመውደቅ ትገደዳለች። እውነተኛ ድል የሚገኘው ከፍ ብሎ በመነሳት ውስጥ እንጂ ከሚነዘንዙህ ጋር ግብግብ በመፍጠር አይደለም፤ ለአሉባልተኞች መልስ በመስጠትም አይደለም። ስላንተ ስያወሩ ውለው ቢያድሩ እንኳን እንዳላየህ፣ እንዳልሰማህ ሆነህ ዝም በላቸው። ንስሯ ተዋግታ አላሸነፈችም። በቀላሉ ከፍ በማለቷ ብቻ ቁራ ራሱን ሊያጠፋ ችሏል። 


ይህንን እወቅ፦ ሌሎች ይናቁህ፣ ይናገሩ፣ ይውቀሱህ፣ ይተቹህ፣ ይሳለቁ።  አንተ ግን እነሱን ለመገዳደር ስባል ጊዜ አታባክን፤ የፈለጉትን ያድርጉ። ይልቁን ለማደግ ፣ ለመራመድ ፣ አዲስ ከፍታ ላይ ለመድረስ ተንቀሳቀስ። 


ምክንያቱም እውነታው እዚህ ጋር ነው፡- ሰዎች አንተ የደረስክበት ከፍታ  ላይ መድረስ አቅቷቸው ይተዉሃል። ምንም ሳይሆን ከፍታህ ብቻ ጩኸታቸውን ጸጥ ያደርጋል። ወደ ታች ለመነታረክ ዝቅ አትበል፤ ወደ ላይ ማደግህን ቀጥል!    

No comments:

Post a Comment

popular post

Result Portal