Result Portal

ሃ ገ ሬ


አገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
አገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ፣
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።
                     {ሰአሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ}

 

ሀገሬ ከበዳት

     




ሀገሬ ከበዳት

​የተማሩ ድሆች፤

መሃይም ሀብታሞች፤

          ሰካራም ሃያሲ፤

         ጉርስ ያጣ ደራሲ፤

ዘራፊ ነጋዴ፤

ሰላም ጠል ወንበዴ፤

        ዘረኛ ካደሬዎች፤

       ህልም አልባ መሪዎች፤

ሆድ አደር ሰባኪ፤

ዉሸታም አምላኪ፤

          ቆብ ቀዳጅ መነኩሴ፤

         ተሳዳቢ ቄሴ፤

ትቢተኛ ሼሆች፤

ግር ባይ አማኞች፤

       አስመሳይ ተዋናይ፤

      የዳኛ ቄል አባይ፤

እኒህ ሁሉ ጉዶች አገር ተሸክማ፤

እንዴት ከፍ ትበል? ከቶ እንዴትስ ትልማ?

የእንግዴ ልጅ

 



​🔍 «የእንግዴ ልጅ» — ለመሆኑ ስሙ ከወዴት መጣ?

​ብዙዎቻችን በዕለት ተዕለት ውይይታችን ውስጥ የምንጠቀመው «የእንግዴ ልጅ» የሚለው ስያሜ፣ ለብዙዎች ጥያቄና ውዝግብ ሲፈጥር ይስተዋላል። "ለመሆኑ ከራሷ አካል ለወጣው ልጅ እንዴት ‘እንግዳ’ የሚል ስም ይሰጠዋል?" የሚሉ ጥያቄዎችም ይነሳሉ።

​ለመሆኑ የዚህ ስያሜ ምስጢር እና ከጀርባው ያለው አስደናቂ ተፈጥሯዊ እውነት ምንድን ነው? እስቲ አብረን እንመርምረው!

​1. «እንግዳ» — ጊዜያዊ ማረፊያ!

​በቋንቋችን «እንግዳ» ማለት ወደ አንድ ቤት ለተወሰነ ጊዜ መጥቶ የሚቆይ፣ የቤቱ ዘላቂ አካል ያልሆነ አካል ነው።

  • ጊዜያዊ ተልዕኮ፦ የእንግዴ ልጅ (Placenta) በማህፀን ውስጥ የሚፈጠረው ፅንሱ ማደግ ሲጀምር ብቻ ነው። ሕፃኑ በሰላም ተወልዶ ወደዚህ ዓለም ሲቀላቀል፣ የእንግዴ ልጅም ተልዕኮውን ጨርሶ አብሮ ይወጣል። እንደ ማንኛውም የአካላችን ክፍል ሁልጊዜ አብሮን አይኖርም።
  • የጊዜያዊ «ድንኳን» ሚና፦ ሕፃኑ በሆድ ውስጥ እያለ የሚመገብበት፣ የሚተነፍስበት እና የሚጠበቅበት ጊዜያዊ ማረፊያ ወይም «የእንግዳ መቆያ» በመሆኑ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

​2. በሕክምናው ዓለም ያለው «እንግዳነቱ»!

​ይህ ደግሞ ይበልጥ አስደናቂው ክፍል ነው! በሳይንሱ ዓለም የእንግዴ ልጅ የእናትየዋ ዘላቂ የአካል ክፍል አይደለም።

  • የራሱ DNA ያለው አካል፦ የእንግዴ ልጅ የሚፈጠረው ከእናቷ ህዋሳት ሳይሆን፣ ከራሱ ከፅንሱ ህዋሳት ነው። የራሱ የሆነ የጂን (DNA) መዋቅር አለው።
  • ​ስለዚህ በሳይንስም ቢሆን በማህፀን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ተላክኮ የሚቆይ «እንግዳ አካል» እንጂ የእናትየዋ አካል ተደርጎ አይወሰድም።

​💡 ባጭሩ ሲጠቃለል…

​«የእንግዴ ልጅ» የተባለው ልጅን በማራቁ ወይም በመግፋቱ ምክንያት ሳይሆን፤ ፅንሱ ወደዚህ ዓለም ከመምጣቱ በፊት በማህፀን ውስጥ እንደ «እንግዳ» የሚቆይበት እና ተልዕኮው ሲያበቃ የሚሸኝ ጊዜያዊ የተፈጥሮ ድንቅ ስራ በመሆኑ ነው!

​📌 እርሶስ ምን ያስባሉ?

ይህ ስያሜ ተስማሚ ሆኖ አግኝተውታል ወይንስ ሌላ የሚገልጸው አማራጭ ስም ቢኖረው ይመረጣሉ? አስተያየትዎን ከታች ያጋሩን! 👇

(ጽሑፉ ከተመችዎ ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ እውቀቱን ያጋሩ!)


ስልጣንና ጣዕሙ ክፍል ሦስት

                        

                    የጥርጣሬ ጥላ 

የቢሮው ስልክ ተዘጋ። ታምራት ግን አሁንም ስልኩን እንደያዙት በዴንጋጤ እና ግራ በመጋባት

ቆመዋል። ያ ዴምፅ... ያ ዴምፅ ጆሯቸው ውስጥ እያስተጋባ ነው። "ታምሬ" የሚሇውን ቃሌ

የሚጠቀመው አንዴ ሰው ብቻ ነበር። ግን እሱ ከሃያ ዓመት በፊት በነበረው በዚያ አስከፊ ምሽት

መሞቱን በዓይናቸው አይተዋል። ታዱያ ዛሬ ከመቃብር የወጣው ማን ነው?

ረዳታቸው በሩን ከፍቶ ገባ። "ጌታዬ፣ ለምሽቱ ግብዣ የሚለበሰው ልብስ ተዘጋጅቷል። እንዱሁም የክብር

እንግድቹ ዝርዝርም..."

"ውጣ!" ብለው ጮኹ ታምራት። ረዳቱ ደንግጦ ወደኋላ አፈገፈገ። ታምራት አሁን ማንም ሰው

እንዲቀርባቸው አይፈልጉም። በቢሮው ውስጥ ያለት ዘመናዊ ካሜራዎች እንኳ እሳቸውን የሚሰልሉ

መሰላቸው። ያ ቢጫ ፖስታ ውስጥ የነበረው ፎቶ የያዘው ሚስጥር ቀላል አይደለም። በፎቶው ላይ

ካለት አራት ሰዎች መካከሌ ዛሬ በሕይወት ያሉት እሳቸውና ላላኛው ጓደኛቸው አቶ ክፍሌ ብቻ

ናቸው።

ክፍሌን ለማግኘት ወዲያውኑ ስሌካቸውን አነሱና ደወለ። ክፍሌ አሁን የትልቅ ዴርጅት ባለቤት

ቢሆንም፣ በታምራት  ስልጣን ጥላ ስር የሚኖር ሰው ነው።

"ክፍሌ፣ ደብዳቤ ደርሶሃል?" አለ ታምራት። ድምፃቸው ይንቀጠቀጣል።

"ምን አይነት ደብዳቤ ታምሬ? ምንም አልደረሰኝም" አላቸው ክፍሌ። "ምነው ደነገጥክ? ዛሬ ምሽት

ታላቁን ድልህን የምታከብርበት ግብዣ አይደለም ወይ?"

"ክፍሌ... ፎቶው ተመልሶ መጥቷል። ያ የጫካው ፎቶ!"

በሌላኛው ወገን ረጅም ዝምታ ሰፈነ። የክፍሌ ትንፋሽ ሲቆራረጥ ይሰማል። "ማን? ማን ነው የላከው? 

እሱ... እሱማ ሞቷል አይደል?"

"አላውቅም። ግን ዛሬ ምሽት ግብዣው ላይ እመጣለሁ ብሎኛል። ክፍሌ፣ ይህ ሚስጥር ከወጣ

ሁለታችንም እናልቃለን። ያ ሁለ ህዝብ ፊት የምናሳየው ክብር በአንድ ቀን አመድ ይሆናል" አለ።

ታምራት ስሌኩን ዘግተው ወደ መስኮቱ ተመለሱ። አሁን መስኮቱ ላይ የሚታያቸው ያንቋሸሹትና

የናቁት ህዝብ አይደለም። በየጥላው ስር ሆነው የሚከታተሏቸው ጠላቶች ናቸው። ስልጣን ጣፋጭ

ነበረች፤ አሁን ግን ጣዕሟ ወደ መራራነት እየተቀየረ ነው።

ምሽቱ ደረሰ። የከተማው ባለስልጣናትና ባለሀብቶች በታምራት ግቢ ውስጥ ተሰብስበዋል። ታምራት

በግዳጅ ይመስል እየሳቁ እንግዶችን ይቀበላሉ። ነገር ግን ዓይኖቻቸው የሚፈልጉት አንድን ሰው ነው። በሕዝቡ

መሀል ሆኖ በንቀት የሚመለከታቸውን፣ ያንን የድሮ ሚስጥር የያዘውን ሰው።

በዚህ መሀል አንድ ግዙፍ ሰው ወደ ታምራት ቀረበ። እጁን ለሰላምታ ዘረጋ። ታምራት ሰውየውን

ሲያዩት የያዙት የወይን ብርጭቆ ከእጃቸው አምልጦ መሬት ላይ ተከሰከሰ።


                                                                 ይቀጥላል....

ትናንሽ እርምጃዎች

 

   

​ትልቅ ተራራን ለመናድ መጀመሪያ ትናንሽ ድንጋዮችን ማንሳት መጀመር ይኖርብሃል። ዛሬ የምታደርጋት አነስተኛ ጥረት፣ የምትማራት አዲስ ክህሎት ወይም የምትጀምራት ትንሽ ስራ ቀላል ልትመስል ትችላለች። ነገር ግን የነገው ትልቅ ስኬትህ መሠረት እሷው ነች። በሂደቱ ላይ እምነት ይኑርህ፤ ዛሬ የምትዘራው ዘር ነገ ማማሩ አይቀሬ ነው!

​🌱 በትናንሽ ጅምሮች አትፈር፣ ታገስ፣ በየቀኑ ጥቂት እርምጃ ወደፊት ተራመድ።

popular post

Result Portal