ስልጣንና ጣዕሙ ክፍል ሦስት

                        

                    የጥርጣሬ ጥላ 

የቢሮው ስልክ ተዘጋ። ታምራት ግን አሁንም ስልኩን እንደያዙት በዴንጋጤ እና ግራ በመጋባት

ቆመዋል። ያ ዴምፅ... ያ ዴምፅ ጆሯቸው ውስጥ እያስተጋባ ነው። "ታምሬ" የሚሇውን ቃሌ

የሚጠቀመው አንዴ ሰው ብቻ ነበር። ግን እሱ ከሃያ ዓመት በፊት በነበረው በዚያ አስከፊ ምሽት

መሞቱን በዓይናቸው አይተዋል። ታዱያ ዛሬ ከመቃብር የወጣው ማን ነው?

ረዳታቸው በሩን ከፍቶ ገባ። "ጌታዬ፣ ለምሽቱ ግብዣ የሚለበሰው ልብስ ተዘጋጅቷል። እንዱሁም የክብር

እንግድቹ ዝርዝርም..."

"ውጣ!" ብለው ጮኹ ታምራት። ረዳቱ ደንግጦ ወደኋላ አፈገፈገ። ታምራት አሁን ማንም ሰው

እንዲቀርባቸው አይፈልጉም። በቢሮው ውስጥ ያለት ዘመናዊ ካሜራዎች እንኳ እሳቸውን የሚሰልሉ

መሰላቸው። ያ ቢጫ ፖስታ ውስጥ የነበረው ፎቶ የያዘው ሚስጥር ቀላል አይደለም። በፎቶው ላይ

ካለት አራት ሰዎች መካከሌ ዛሬ በሕይወት ያሉት እሳቸውና ላላኛው ጓደኛቸው አቶ ክፍሌ ብቻ

ናቸው።

ክፍሌን ለማግኘት ወዲያውኑ ስሌካቸውን አነሱና ደወለ። ክፍሌ አሁን የትልቅ ዴርጅት ባለቤት

ቢሆንም፣ በታምራት  ስልጣን ጥላ ስር የሚኖር ሰው ነው።

"ክፍሌ፣ ደብዳቤ ደርሶሃል?" አለ ታምራት። ድምፃቸው ይንቀጠቀጣል።

"ምን አይነት ደብዳቤ ታምሬ? ምንም አልደረሰኝም" አላቸው ክፍሌ። "ምነው ደነገጥክ? ዛሬ ምሽት

ታላቁን ድልህን የምታከብርበት ግብዣ አይደለም ወይ?"

"ክፍሌ... ፎቶው ተመልሶ መጥቷል። ያ የጫካው ፎቶ!"

በሌላኛው ወገን ረጅም ዝምታ ሰፈነ። የክፍሌ ትንፋሽ ሲቆራረጥ ይሰማል። "ማን? ማን ነው የላከው? 

እሱ... እሱማ ሞቷል አይደል?"

"አላውቅም። ግን ዛሬ ምሽት ግብዣው ላይ እመጣለሁ ብሎኛል። ክፍሌ፣ ይህ ሚስጥር ከወጣ

ሁለታችንም እናልቃለን። ያ ሁለ ህዝብ ፊት የምናሳየው ክብር በአንድ ቀን አመድ ይሆናል" አለ።

ታምራት ስሌኩን ዘግተው ወደ መስኮቱ ተመለሱ። አሁን መስኮቱ ላይ የሚታያቸው ያንቋሸሹትና

የናቁት ህዝብ አይደለም። በየጥላው ስር ሆነው የሚከታተሏቸው ጠላቶች ናቸው። ስልጣን ጣፋጭ

ነበረች፤ አሁን ግን ጣዕሟ ወደ መራራነት እየተቀየረ ነው።

ምሽቱ ደረሰ። የከተማው ባለስልጣናትና ባለሀብቶች በታምራት ግቢ ውስጥ ተሰብስበዋል። ታምራት

በግዳጅ ይመስል እየሳቁ እንግዶችን ይቀበላሉ። ነገር ግን ዓይኖቻቸው የሚፈልጉት አንድን ሰው ነው። በሕዝቡ

መሀል ሆኖ በንቀት የሚመለከታቸውን፣ ያንን የድሮ ሚስጥር የያዘውን ሰው።

በዚህ መሀል አንድ ግዙፍ ሰው ወደ ታምራት ቀረበ። እጁን ለሰላምታ ዘረጋ። ታምራት ሰውየውን

ሲያዩት የያዙት የወይን ብርጭቆ ከእጃቸው አምልጦ መሬት ላይ ተከሰከሰ።


                                                                 ይቀጥላል....

No comments:

Post a Comment

popular post

Result Portal