ሳያቋርጡ_ጥረት_ማድረግ (ወጥነት) (consistency

 

                        


በተራራው ጫፍ ላይ የመውጣት ዓላማ ኖሮህ ከተራራው ስር ተቀምጠህ ሽቅብ ወደላይ ስታየው መውጣት ፈፅሞ የሚቻል ላይመስልህ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከተቀመጥክበት ተነስተህ የመጀመሪያውን እርምጃ ስታደርግ ከተቀመጥክበት አንድ እርምጃ እየራቅክ ወደ ተራራው ጫፍ አንድ እርምጃ እየቀረብክ ነው ማለት ነው፡፡ 

እርምጃህን ሳታቋርጥ ሽቅብ መጓዝህን ብትቀጥል ከብዙ እርምጃዎች በኋላ ራስህን በተራራው ጫፍ ላይ ልታገኝ ትችላለህ፡፡ እንደት ባለ ሁኔታ ይኼንን አስፈሪ ተራራ እንደወጣህ ከተራራው ጫፍ ላይ ሆነህ ትገረማለህ፡፡

ዛሬ የ2018 ዓ.ም ሐምሌ 3 ነው፡፡ ዓመቱ እያለቀ ነው። በዚህ ዓመት አሳካዋለው ብለህ ያቀድከውን ዕቅድ ገምግመህ ለቀጣዩ የዓመት ዕቅድህን አንድ ብለህ ማቀድ እና መዘጋጀት ትችላለህ፡፡ በዚህ ውሳኔህ ከፀናህና ሳታቋርጥ "consistently" ዕቅድህን መተግበር ከቻልክ የዓመቱን ዕቅድህን ከማሳካት ወደ ኋላ አትመለስም፡፡ 

የዛሬው ጥረትህ ብቻዋን ከምንም የማትቆጠር ትንሽዬ ተግባር ሆና ልታገኛት ትችላለህ፡፡ ነገር ግን የየቀኑ ትንንሽ ተግባራት ድምር ውጤት ትልቅ ተግባር ይሆናል። ስለዚህ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ለማሳካት ስላሰብከው ትልቅ ውጤት ማሰብህን ለጊዜው አቁመህ የዛሬ ተግባርህን ለራስህ #ታማኝ ሆነህ መተግበር ጀምር፡፡ 

ቀስ በቀስ ወደ ስኬትህ እየቀረብክ አሁን ካለህበት እየራቅክ እንደሚትሄድ አውቀህ ዛሬውኑ ጀምር፣ ነገም ቀጥልበት፣ ከነገ ወዲያም አታቋርጥ፡፡ ከሳምንት ወደ ሳምንት፣ ከወር ወደ ወር ሳታቋርጥ ጥረት በማድረግ ከተነሳህበት መነሻ እየራቅክ ወደ መዳረሻህ እየቀረብክ መምጣትህ የማይቀር ነው፡፡ 

እግዚአብሔር በነገር ሁሉ መከናወንን ይስጠን!

No comments:

Post a Comment

popular post

Result Portal