ታማኛለች ቀርፋፋ ነው እያለች ፤ አላወቀችም ከብዙ ቀን ጥርቅም በኋላ መራመድ እንደሆነልኝ  ፤ ተዓምር ሆኖ ባርቆብኝ ፣ ደክሞኝ እየተራመድኩ እንደሆነ ብታውቅ መንቀራፈፌ ሳይሆን መራመዴ ትንግርት ይሆንባት ነበር!

ደግሞ  አሮጌ ጨርቅ ማጥለቄ  ደህይቼ  መስሏታል ፤ ከጎዳና ላይ ተነስቼ  ከብጭቅጫቂ ጨርቅ ወደ አሮጌ ጨርቅ ማደጌን ብታውቅ ደህይቼ ሳይሆን እያለፈለኝ መሆኔን ትገነዘብ ነበር።

ትክ ብዬ ማየቴ  ድፍረት ነው የመሰላት ፤ አንገቴን ደፍቼ መኖሬን ብታውቅ ቀና ከማለት አድጌ በልበ-ሙሉነት ማየቴ ድፍረት ሳይሆን ልበ-ሙሉነቴ አድጎ እንደሆነ ትመሰክርልኝ ነበር ። 

እግረመንገዱን የመጣ መዛኝ እየመዘነ ነው የሚያስቀን !

ችላ ስትለኝ ችላ ማለቷን ከቁብ ያለመቁጠር  ንቀት  ነው የመሰላት  ግን አይደለም ፤
የስህተታችን ጅማሬ በሁሉም ሰው ተቀባይነት ለማግኘት መዳከር ነው የሚለው ጥበብ ገብቶኝ እንጂ ። 

እኔ ግን ትግሌ ከራሴ ትናንት ጋ ነው!!!
              
@keye_ber

No comments:

Post a Comment

popular post

Result Portal