ፍቅር ነበር..? አልኳት...
(የቅሬታ ፈገግታ ፈገግ አለችልኝ)
እኔንጃ ግን በጣም ተንከባካቢ ሰው ነበር አለች። አቀርቅራ ጣቶቿን መደባበስ ጀመረች።
አሁንም ትወጂዋለሽ ...
''ኸረረ''..አፈጠጠችብኝ
''ሌላ መመኘቱን ባወኩ ቀን የኔ የነበረውን ማንነቱን ለሌላ ሲሰጥ ባየሁ ቅፅበት አምርሬ ተፀየፍኩት!
ግን...''
ቃላቶቿን በእንጥልጥል ተወቻቸው ....
ከአንደበቷ ከወጡት የችኮላ ቃላት ይልቅ የልቧ ህመም ይረብሽ ነበር
በለሆሳስ ''ግን ....አሁን አልወደውም'' አለች
ከአይኔ ስትሸሽ ይታወቀኛል
አቀረቀረች....እንባዋ እጆቿ ላይ ተንጠባጠበ
ዝም ብዬ ማየቴ ፀፀት ቢሰማኝም
ለፍቅር ምን ማፅናኛ አለው...?

No comments:
Post a Comment